የሶማሌ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች፣የሀይማኖት አባቶች፣ የጎሳ መሪዎች( ሱልጣኖች፣ኡጋዞችና ገራዶች) እና ምሁራን የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ
አዲስ አበባ ሐምሌ 29 .2017ዓ.ም /ኦገስት 5. 2025 ዓ.ም እንደሚታወቀው የሶማሌ ክልል በተለያዩ ግዜያቶች የተለያዩ ፈታኝ እና አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ያሳለፈ ክልል ሲሆን፤ እነዚህ አስቸጋሪ ሁኔታዎች የክልሉን ማህበረሰብ ህልዉናና የአኗኗር ዘይቤን በቀጥታ ተፅዕኖ ያሳደረና ለፖለቲካዊ፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ የዘፈቀ ሁኔታዎች እንደነበሩ ፀሀይ የሞቀው ሀቅ ነው፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች የተፈጠሩት በተለያዩ ግዜያቶች ክልሉን የመሩት የክልሉ የፖለቲካ ልሂቃንና አስተዳደሮች