አንድ ድርጅት እንዴት የፓርቲ መሪና የፓርቲ ሊቀ መንበር ይኖረዋል?
የ #ኢዜማ የአደረጃጀት መርህ በሀገርና በድርጅት ፍላጎትና ጥቅም መሀከል ሊኖር የሚገባውን ጤናማ ግኙነት ከማረጋገጥ አንጻር፤ በሀገራችን በተለይ በምርጫ ስም ሥልጣን መያዝ ከተጀመረበት ወቅት አንስቶ በአሸናፊነት እራሳቸውን ያስቀመጡ ድርጅቶች በሀገርና ሕዝብ ላይ ካደረሱት ከፍተኛ ጉዳቶች መሀከል አንዱ የድርጅትን ፍላጎትና ጥቅም ከሀገር ፍላጎትና ጥቅም ለይቶ ካለማየት የደረሰው ጉዳት ነው። የመጀመሪያው የጉዳት ዓይነት በማናቸውም በተረጋጉ ሀገሮች የሚታየውን መንግሥትን