የሕዝቡን የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች የመመለሱን ተግባር ለማጠናከር የገቢ አቅምን ማሳደግ ያስፈልጋል – ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን
አሶሳ፤ ሐምሌ 19/2017 በክልሉ የሕዝቡን የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች የመመለሱን ተግባር ለማጠናከር የገቢ አቅምን ይበልጥ ማሳደግ እንደሚያስፈልግ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ተናገሩ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በከሰዓት ውሎው ርዕሰ መስተዳድሩ ባቀረቡት የ2017 በጀት ዓመት ሪፖርት ዙሪያ የምክር ቤት አባላት ጥያቄ እና አስተያየት አቅርበዋል። የምክር ቤቱ አባላት የመንገድ፣ የጤና እና ሌሎች

