ለሽብር ተልዕኮ የተመለመሉ 82 የአይ ኤስ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 8/2017(ኢዜአ)፦ለሽብር ተልዕኮ የተመለመሉ 82 የአይ ኤስ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ። የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፤ በፑንትላንድ የሚንቀሳቀሰው የአይ ኤስ የሶማሊያ ክንፍ በተለያዩ ሀገራት እንዲሁም በኢትዮጵያ ለመስፋፋትና የሽብር ቡድኑን ሴሎች ለመመስረት የሚያደርገውን ጥረት በተመለከተ የመረጃ ስምሪትና ጥናት ሲደረግ ቆይቷል፡፡ የአይ ኤስ የሶማሊያ ክንፍ በኢትዮጵያ የሽብር