በአፍሪካ የህጻናት የማንበብ እና መረዳት ችግርን ለማጥፋት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል- የአፍሪካ ህብረት
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 14/2017 , የአፍሪካ ህብረት በአህጉሪቱ ህጻናት ያለባቸውን የማንበብ እና የመረዳት ችግር እ.አ.አ በ2035 ለማስቀረት በልዩ ትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ አስታወቀ። በአፍሪካ በቀዳማይ ልጅነት ዘመን የህጻናት መሰረታዊ የማንበብ፣ የመጻፍ እና የሂሳብ ክህሎቶችን ማላቅ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ከፍተኛ የባለድርሻ አካላት አውደ ጥናት ሐምሌ 15 እና 16 ቀን 2017 ዓ.ም በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ይካሄዳል።