ኢትዮጵያ ማንሠራራት በጀመረችበት እና ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በተመረቀበት ጊዜ ለሚከበረው አዲስ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ
ያለፈው ዓመት ፈጣሪ ከጎናችን፣ ስኬት በደጃችን መሆኑን ያየንበት ዓመት ነበር፡፡ በግብርና፣ በቱሪዝም፣ በማዕድን፣ በአምራችነት እና በአይሲቲ ዘርፎች ያስመዘገብናቸው ውጤቶች ይሄንን ይመሰክራሉ፡፡ ኢትዮጵያን ያህል ሀገር፣ ኢትዮጵያውያንን ያህል ሕዝብ ይዘን በትጋት ከሠራን፣ ከዚህ በላይ ድል ልናሳካ እንደምንችል ምስክራችን የሕዳሴ ግድብ ነው፡፡ ከእርግዝና ወራት ሁሉ እጅግ አስቸጋሪዎቹ፣ እጅግ አስፈሪዎቹ እና እጅግ ፈታኞቹ የመጨረሻዎቹ ሰዓታት ናቸው ይባላል፡፡ በሕዝብ ልብ