የዓለም የኢኮኖሚ ሥርዓትን ሚዛናዊ ለማድረግ የተመሰረተው ብሪክስ
የዓለም የኢኮናኖሚ ሥርዓት ለምዕራባውያን ያደላ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ይህንን የኢኮኖሚ ሥርዓት ሚዛናዊ ማድረግ ይገባል በሚል ነበር ብሪክስ እኤአ በ2006 የተመሠረተው፡፡ መስራቾቹ ደግሞ ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ እና ቻይና ሲሆኑ፣ ደቡብ አፍሪካ እኤአ በ2010 ጥምረቱን ተቀላቅላለች፡፡ ጥምረቱ የተመሰረተበት ዋና ዓላማ ተባብሮ በመስራት ሀገራቱ ኢኮኖሚያቸውን እንዲያሳድጉ ማድረግ ነው፡፡ የነዚህ ሀገራት ኢኮኖሚ በፍጥነት እያደገ በመምጣቱ ‘ታይገር ኤኮኖሚ’ የሚል ስያሜም አግኝቷል፡፡

