አዲስ አበባ፣ መስከረም 3 (HornCurrent) – የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በ“እመርታ ቀን” እንደተጠራው ልዩ ቀን ሕዝቡን በመመልከት መልዕክት አቀረቡ።
“እመርታ ለዘላቂ ከፍታ” በሚል መልዕክታቸው ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የታሪክ እድልና የመንገዳችን ታላቅነት ሲያሳስቡ እንዲህ ብለዋል፦
“የወረስነው ዕዳ ብዙ፤ የምንጓዝበት መንገድ ረዥም፤ ሕዝባችንም ፍላጎት ሰፊ ነው፡፡ ቀስ በቀስ በሚደረግ የተለመዶ ጉዞ ወደምንፈልገው የብልጽግና ምእራፍ አንደርስም። ስለዚህ ፈጠራና ፍጥነት ወሳኞች ናቸው።”
በመልዕክቱ ውስጥ በተለይ “ከተለመደው መንገድ መውጣት፣ ከተለመደው ጊዜ በላይ መሥራት፣ ከተለመደው ዋጋ በላይ መክፈል” ብለው እንደሚያስፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታወሱ።
ዓላማውም ከአንድ ምዕራፍ ወደ ሌላ ምዕራፍ መሻገር ሳይሆን “ከትናንት ዘለን ወደ ነገ መድረስ” መሆኑን በግልፅ ቃላት ገልጸዋል።