August 11, 2025
Africa Amharic News

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የመራጭ ተመራጭ ውይይት ተጀመረ

ነሐሴ 04 ፣ 2017 ዓ.ም፤ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ሀዲያ ዞን ኮንትብ 03 ምርጫ ክልል የ2017 ዓ.ም. የክረምት የመራጭ ተመራጭ ህዝብ ወክልና ሥራ ተጀምሯል።

የዞኑ ዋና አስተዳደሪ እና ሌሎች አስፈጻሚ አካላት በተገኙበት የክረምት የመራጭ ህዝብ የውክልና ሥራ የጋራ መድረክ መካሄዱን የተከበሩ ወ/ሮ ሙሉነሽ ላሞሬ ገልጸዋል፡፡

የጋራ መድረኩን በመከተል በኮንተብ 03 ምርጫ ክልል ካሉ ሦስት ወረዳዎችና የአንድ ከተማ አስተዳደር የበጀት ዓመቱ ክንውን ሪፖርት ለሁለቱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ግንዛቤ ተፈጥሯል ብለዋል፡፡

በመቀጠልም በኮንተብ 03 ምርጫ ክልል አንዱ በሆነው የጎንቦሮ ወረዳ ክላስተር የመራጭ ህዝብ ውይይት መደረጉን እና በውይይቱ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ተሳታፊዎች መገኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

ከዚሁ የምርጫ ክላስተር በየካቲት 2017 ዓ.ም. በተካሄደው የህዝብ ውክልና ውይይት ወቅት የተነሡ ከውሀ፣ ከመንገድ መሠረተ ልማት፣ ከኤሌክትሪክ አገልግሎት አሰጣጥና ማስፋፊያ፣ ከጤና ቁሳቁስ እና መድሃኒት፣ ከአፈር ማዳበሪያ እና ከምርጥ ዘር አቅርቦት፣ ከወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ከፍጆታ ምርት አቅርቦትና ተደራሽነት፣ ከማዕድን ልማት እንዲሁም ከሠራተኛ ደመወዝ እና (የትርፍ ሰዓት ክፍያ) ተጠናቆ ያለመከፈ እና የዕዳ ሽግሽግ ጥያቄ ጋር ተያይዞ ያሉ ጉዳዮች በዋናነት በክላስተሩ የተነሡ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች መሆናቸው ተመላክቷል።

በየደረጃው በሚገኙ አካላት የተመለሱ እና የ2018 ዓ.ም የመንግሥት በጀት አካል ሆነው በዕቅድ የተያዙ የመንገድ የውሀ እና ሌሎች የመሠረተ ልማት፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ከፌዴራልና ከክልሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኙ አባላት ማብራሪያ መስጠታቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

በምርጫ ክላስተሩም የሁሉቱ ምክር ቤት አባላትና የወረዳው አጠቃላይ ፖሊስ አባላት ችግኝ ተከላ ሥራ ተከናውኗል፡፡

የቀሪ ምርጫ ክለስተሮች በወጣው መርሀ ግብር መሠረት ውይይቱ እንደሚካሄድም ተገልጿል፡፡

Source: @FDREHOPR

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *