August 3, 2025
Amharic Ethiopia News

የዓለም የኢኮኖሚ ሥርዓትን ሚዛናዊ ለማድረግ የተመሰረተው ብሪክስ

የዓለም የኢኮናኖሚ ሥርዓት ለምዕራባውያን ያደላ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ይህንን የኢኮኖሚ ሥርዓት ሚዛናዊ ማድረግ ይገባል በሚል ነበር ብሪክስ እኤአ በ2006 የተመሠረተው፡፡

መስራቾቹ ደግሞ ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ እና ቻይና ሲሆኑ፣ ደቡብ አፍሪካ እኤአ በ2010 ጥምረቱን ተቀላቅላለች፡፡

ጥምረቱ የተመሰረተበት ዋና ዓላማ ተባብሮ በመስራት ሀገራቱ ኢኮኖሚያቸውን እንዲያሳድጉ ማድረግ ነው፡፡

የነዚህ ሀገራት ኢኮኖሚ በፍጥነት እያደገ በመምጣቱ ‘ታይገር ኤኮኖሚ’ የሚል ስያሜም አግኝቷል፡፡

አሁን ላይ ብሪክስ ተጨማሪ ሀገራትን እያቀፈ ወደ ወደ ብሪክስ ፕላስ ተቀይሯል፤ ኢትዮጵያ፣ ኢንዶኖዢያ፣ ግብፅ፣ ኢራን፣ ሳውዲ ዓረቢያ እና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ያሉ ሀገራት የብሪክስ አባል መሆን ችለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ እየተካሄደ ባለው 17ኛው የብሪክስ ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከብራዚል ፕሬዚዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ እና ከቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር መክረዋል፡፡

ውይይቱ ሀገራቱ በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ዙሪያ የቆየውን ትብብራቸውን ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡

ፀሃፍ: ናትኔል ሞከኔን

EBC #ebcdotstream #BRICS #BRICSSummit

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *